በየአመቱ፣ በፌደራል በቢልዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮች ለሆስፒታሎች፣ ለእሳት መከላከያ ክፍል፣ ትምህርት ቤቶች፣ መንገዶች፣ ለሌሎች መሰረተ ልማቶች የገንዘብ ድጋፍ የሚያከናውነው በዚህ በመመስረት ነው።
ህዝብ ቆጠራ ውጤቶቹ እያንዳንዱ ክፍለ-ግዛት በኮንግረስ ውስጥ የሚኖረውን የወንበር ብዛት ይወስናሉ፣ እንዲሁም የምርጫ ጣብያ ድንበር ለመወሰን ይጠቅማል።
ህዝብ ቆጠራው መካሄድ እንዳለበት በዩናይድ ስቴትስ ሕገመንግስት ተደንግጓል: አንቀጽ 1, ክፍል 2, አሜሪካ በየ 10 ዓመት አንድ ጊዜ የህዝብ ቆጠራ መከናወን እንዳለበት ይደነግጋል። የመጀመሪያው ህዝብ ቆጠራ የተከናወነው በ1790 ነበር ።
ህዝብ ቆጠራ ቢሮው የእርስዎን ምላሾች እንዲጠብቅ እና በሚስጢር እንዲይዝ በሕግ ይገደዳል። በእርግጥ፣ እያንዳንዱ ሰራተኛ የእርስዎን መረጃ መቼም ቢሆን እንደሚጠብቅ ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።
በአሜሪካ አንቀጽ 13 ስር፣ ህዝብ ቆጠራ ቢሮው ማናቸውም የእርስዎን ማንነት፣ መኖሪያ ቤት፣ ወይም የንግድ ስራዎ የሚገልፅ ማንኛውንም መረጃ ለሕግ አስፈጻሚ አካላት እንኳን ሳይቀር አሳልፎ መስጠት አይችልም። ህጉ እንደሚያረጋግጠው ግላዊ መረጃዎ እና መልስዎ ጥበቃ እንደሚደረግለት እና መልስዎ በማንኛውም የመንግስት ተቋም ወይም ፍርድ ቤት ጥቅም ላይ እንደማይውል ያስረዳል ።
ይህ የተለመደ የ 2020 ህዝብ ቆጠራ አካል ነው። የህዝብ ቆጠራ ሰራተኞች ለጥቂት የተለያዩ አላማዎች በአከባቢዎ ሊመለከቷቸው ይችላሉ:
በሜይ 2020፣ ፣ የህዝብ ቆጠራ ሰራተኞች ለ2020 ህዝብ ቆጠራ ምላሽ ያልሰጡ ቤቶችን መጎብኘት ይጀምራሉ ይህም ሁሉም ሰው መቆጠሩን ለማረጋገጥ ነው ።